በኃያላን ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።
በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
በመሪዎች ከመመካት ይልቅ፥ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
ጐልማሳ መንገዱን በምን ያቀናል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።
ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ ጌታንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
አሦርም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፥ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻል ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።
በእጅህ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህ ትከሻቸውን ሁሉ ቆረጥህ፤ በአንተ ላይ ሲደገፉ ተሰበርህ ወገባቸውንም ሁሉ አንቀጠቀጥህ።”
አሁንም፦ “ጌታን አልፈራንምና ንጉሥ የለንም፤ ንጉሥስ ለእኛ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ።