እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥
መዝሙር 115:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አሰበን፥ ይባርከንማል፥ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፥ የአሮንንም ቤት ይባርካል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ያስበናል፤ ይባርከናልም፤ እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤ የአሮንንም ቤት ይባርካል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያስታውሰናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤ የእስራኤልን ሕዝብና የእግዚአብሔርን ካህናት ሁሉ ይባርካል። |
እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥
ያዕቆብ ሆይ፥ አንተም እስራኤል፥ አገልጋዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ አንተም አገልጋዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፥ በእኔ ዘንድ ያልተረሳህ ትሆናለህ።
እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ “ጌታ ሆይ! ምንድነው?” አለ። መልአኩም አለው “ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።