ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥ ዓሦቻቸውንም ገደለ።
ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ ዓሦቻቸውንም ፈጀ።
የወንዞቻቸውንም ውሃ ወደ ደም ለወጠ፤ ዓሣዎቻቸውንም ሁሉ ገደለ።
በሥራቸውም አነሣሱት ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
ወንዞቻቸውንም ወደ ደም ለወጠ፥ ምንጮቻቸውን እንዳይጠጡ።
በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።
ሁለተኛውም መልአክ ጽዋውን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ ባሕሩም የሞተ ሰው ደም መሰለ፤ በባሕርም ውስጥ ሕይወት ያለው ነፍስ ሁሉ ሞተ።