በሚቀጥለውም ቀን ሰሎሞን ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ፤ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ።
መዝሙር 100:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደስታም ለጌታ ተገዙ፥ በእልልታም ወደ ፊቱ ግቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤ በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት! የደስታ መዝሙር እየዘመራችሁ ወደ እርሱ ፊት ቅረቡ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እዘምራለሁ፥ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፤ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ። |
በሚቀጥለውም ቀን ሰሎሞን ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ፤ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ።
ንጉሡም ሕዝቅያስና ሹማምንቱ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል ጌታን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። በደስታም እያመሰገኑ፥ አጐነበሱም ሰገዱም።
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው አቆመ፤ በጌታ ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑም ክብርም እንዲሰጡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን አቆመ።
እዚያም እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም የራሳቸው ድርሻ ወይም ርስት የሌላቸው በየከተሞቻችሁ የሚኖሩት ሌዋውያን በጌታ በአምላካችሁ ፊት ሐሤት አድርጉ።”
አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፥ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች ጌታ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባርያህና ሴት ባርያህ፥ በአገርህም ደጅ ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሀ አደግና መበለትም በበዓል ደስ ይበላችሁ።