ምሳሌ 7:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው፥ ወደ ሞት ማደርያዎች የሚወርድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቷ ወደ ሲኦል የሚወስድ፣ ወደ ሞት ማደሪያም የሚያወርድ ጐዳና ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርስዋ ቤት የሚወስደው መንገድ ወደ ሞትና ወደ መቃብር የሚያወርድ ጐዳና ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቷ ወደ ሞት ጓዳ የሚያወርድ የሲኦል መንገድ ነው። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥