ምሳሌ 7:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መሥዋዕትንና የደኅንነት ቁርባንን ማቅረብ ነበረብኝ፥ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በቤቴ የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ የስእለቴን መባ አቅርቤአለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የፍቅሬ መሥዋዕት ነው፤ ዛሬ ስእለቴን እሰጣለሁ። |
ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፤ ሰንበቶቻችሁን፤ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም።
ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ማለዳም ነበረ፤ እነርሱም እንዳይረክሱ፥ ይልቁንም የፋሲካን በግ እንዲበሉ በማለት ወደ ገዢው ግቢ አልገቡም።