ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
ምሳሌ 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር፦ “ልብህ ቃሌን በጥብቅ ይያዘው፥ ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤ “ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቴም እንዲህ እያለ ያስተምረኝ ነበር፤ “ቃሌን በሙሉ ልብህ ያዘው፤ ትእዛዞቼንም ፈጽም፤ በሕይወትም ትኖራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦ ቃላችን በልብህ ይኑር፤ ትእዛዞቻችንንም ጠብቅ፥ አትርሳቸውም። |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
ኤርምያስም እንዲህ አለው፦ “አሳልፈው አይሰጡህም። እኔ የነገርሁህን የጌታን ድምፅ እባክህ፥ ስማ ለአንተም የቀና ይሆንልሃል ነፍስህም በሕይወት ትኖራለች።
“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።
በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስታውሳለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድና በእናትህ በኤውንቄ የነበረ ነው፤ አሁን ደግሞ በአንተ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ።
እንዲሁም ከሕፃንነትህ አንሥቶ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ወደሚገኘው መዳን የሚመራህን ጥበብ ሊሰጡህ የሚያስችሉትን ቅዱስ መጻሕፍትን አውቀሃልና።