Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዛሬ እኔ የማዝህ እነዚህን ቃላትም በልብህ አኑር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች በልብህ ያዝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች አትርሳ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እኔም ዛሬ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ይህን ቃል በል​ብህ፥ በነ​ፍ​ስ​ህም ያዝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 6:6
22 Referencias Cruzadas  

ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።


ሕጎቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ከሥርዓቱም አልራቅሁም።


አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።


ከአፍህ የሚወጡትን ፍርዶች ሁሉ በከንፈሮቼ ደገምኳቸው።


የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።


ለዘለዓለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።


የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥ በእርምጃውም አይሰናከልም።


በዚያን ጊዜ እንዲህ አልሁ፦ “እነሆ፥ መጣሁ፥ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፥


በፍጹም ልብህ በጌታ ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፥


በጣቶችህ እሰራቸው፥ በልብህ ጽላት ጻፋቸው።


ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፥ ስሙኝ፤ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፥ በስድባቸውም አትደንግጡ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም እነዚህን ነገሮች ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።


በመልካም መሬት ላይ ያሉት ደግሞ ቃሉን በመልካምና በቅን ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፥ በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።


እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም ያልሆነ፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ፥ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።


“እነዚህን ቃሎቼን፥ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፥ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ።


በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው፤


እንዲህ አላቸው፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ፥ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።


የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤


በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘለዓለም ስለሚሆን እውነት፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos