ምሳሌ 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይታገድም፥ ብትሮጥም አትሰናከልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ ስትሮጥም አትደናቀፍም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥበብ ብትራመድ እርምጃህ አይታገድም፤ ብትሮጥም አትሰናከልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤ በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም። |
በልቅሶ ይወጣሉ፤ እኔንም በመማፀናቸው እየመራሁ እመልሳቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኩሬ ነውና።
ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።