ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓብ መልእክት ደረሰ፤ በዚህን ጊዜ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፤ ስለዚህም እነርሱ ፈጥነው በመንቀሳቀስ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።
ምሳሌ 31:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠጥተው ሕግን እንዳይረሱ፥ የድሀ ልጆችንም ፍርድ እንዳያጐድሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤ የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፍፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ጠጥተው ሲሰክሩ ሕግን ይረሳሉ፤ የተቸገሩትንም ሰዎች መብት ችላ ይላሉ። |
ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓብ መልእክት ደረሰ፤ በዚህን ጊዜ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፤ ስለዚህም እነርሱ ፈጥነው በመንቀሳቀስ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።
“እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክርን መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው፤
በእርግጥ ወይን አታላይ ነው፤ ትዕቢተኛ ሰው በስፍራው አርፎ አይቀመጥም፤ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፤ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።