La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 3:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታ መርገም በክፉ ሰዎች ቤት ነው፥ የጻድቃን ቤት ግን ይባረካል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር ርግማን በክፉዎች ቤት ላይ ነው፤ የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር በክፉ ሰዎች ቤት እርግማንን ያመጣል፤ የደጋግ ሰዎችን ቤት ግን ይባርካል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእግዚአብሔር መርገም በክፉዎች ቤት ነው፥ በጻድቃን ቤት ግን በረከት አለ።

Ver Capítulo



ምሳሌ 3:33
20 Referencias Cruzadas  

የጌታም ታቦት የጌት ሰው በሆነው በዖቤድ ኤዶም ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ጌታም ዖቤድ ኤዶምና ቤተሰቡን ሁሉ ባረከ።


“እነርሱ በውኃ ላይ ተንሳፈው ያልፋሉ፥ ድርሻቸውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፥ ወደ ወይኑ ቦታ መንገድ አይመለሱም።


ይህ እስከ ጥፋት ድረስ የሚበላ እሳት፥ ቡቃያዬንም ሁሉ የሚያቃጥል ነውና።”


እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥ ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።


እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና፥ የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።


በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፥ የክፉዎች አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል።


የኀጥኣን ቤት ይፈርሳል፥ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።


በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ኃይል አለ፥ የኀጥእ ሰው መዝገብ ግን ሁከት ነው።


ጻድቅ ስለ ኀጥእ ቤት ያስባል፥ ኀጥኣንም ለጥፋት እንደ ተገለበጡ።


“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”


መርገሙ ደግሞ፥ የጌታ የአምላካችሁን ትእዛዞች የማትፈጽሙ፥ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።”


እንደ እርሱም ለጥፋት የምትሆን እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።


እናንተ ግን እርም ካደረጋችሁት በኋላ እርም ከሆነው ነገር ራሳችሁን ጠብቁ፤ እርም ከሆነው አንዳች የወሰዳችሁ እንደሆነ የእስራኤልን ሰፈር የተረገመ ታደርጉታላችሁ፥ ታስጨንቁታላችሁም።


ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ፥ እንዲህም በላቸው፦ ‘እስከ ነገ ተቀደሱ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፦ “እስራኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፤ እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።”