አሜስያስ ሆይ! እነሆ፥ አንተም ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ በአገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍትን የሚያስከትል ነገር ለመቆስቆስ ስለምን ትፈልጋለህ?”
ምሳሌ 3:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ክፉ ካልሠራብህ፥ ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም ጕዳት ሳያደርስብህ፣ ያለ ምክንያት ሰውን አትክሰስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም በደል ያላደረሰብህን ሰው ያለ ምክንያት አትክሰሰው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በላይህ የሠራው ክፉ ነገር ከሌለ፥ ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ። |
አሜስያስ ሆይ! እነሆ፥ አንተም ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ በአገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍትን የሚያስከትል ነገር ለመቆስቆስ ስለምን ትፈልጋለህ?”