ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማንኛውም ሌላ ንጉሥ ያላገኘውን ብልጽግናና ክብር አበዛልሃለሁ።
ምሳሌ 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀኝዋ ረጅም ዘመን ነው፥ በግራዋም ባለጠግነትና ክብር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀኝ እጇ ረዥም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ በቀኝ እጅዋ ረጅም ዕድሜን በግራ እጅዋ ደግሞ ብልጽግናንና ክብርን ይዛለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው። ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥ ከአፏ ጽድቅ ይወጣል። ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች። |
ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ እሰጥሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማንኛውም ሌላ ንጉሥ ያላገኘውን ብልጽግናና ክብር አበዛልሃለሁ።
አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን፥ ወንድሞችን፥ እኅቶችን፥ እናቶችን፥ ልጆችንና ዕርሻን መቶ ዕጥፍ የማይቀበል፥ በሚመጣውም ዓለም የዘለዓለም ሕይወት የማይወርስ የለም።
ሰውነትን አካላዊ እንቅስቃሴ ማለማመድ መጠነኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም እንኳ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣውን ሕይወት የተስፋ ቃል ስላለው፥ ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።