ምሳሌ 28:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብቱን በአራጣ ብዛትና በቅሚያ የሚያበዛ ለድሀ ለሚራራ ያከማችለታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራጣ በማበደርና ሰዎችን በመበዝበዝ የሚከብር ሰው ሀብቱ ሁሉ ለድኾች ልግሥና ለሚያደርግ ሰው ይተላለፋል። |
እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፥ ለኃጢአተኛው ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ሥራን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
በአራጣ ቢያበድር፥ ትርፍንም ቢወስድ፥ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም፤ እነዚህን ርኩሰቶች ሁሉ አድርጎአልና በእርግጥ ይሞታል፤ ደሙም በላዩ ላይ ይሆናል።
ድሀ ከመበደል እጁን ቢመልስ፥ አራጣ ወይም ትርፍ ባይወስድ፥ ፍርዴን ቢያደርግ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።