ምሳሌ 28:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ የሚጠነቀቅ ሰው ብፁዕ ነው፥ ልቡን የሚያጸና ግን በክፉ ላይ ይወድቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ዘወትር የሚፈራ ሰው ብፁዕ ነው፤ ልቡን የሚያደነድን ግን መከራ ላይ ይወድቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁልጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የተባረከ ነው፤ እምቢተኛ የሚሆን ሰው ግን ችግር ላይ ይወድቃል። |
እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለች፤ እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል ጌታ። ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።
ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።