ምሳሌ 28:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምሕረትን ያገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአቱን የሚደብቅ ኑሮው አይሳካለትም፤ ኃጢአቱን ተናዝዞ ዳግመኛ ኃጢአት ከመሥራት የሚቈጠብ ግን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛል። |
አቤሴሎምም፥ ኢዮአብን፥ “‘ከገሹር ለምን መጣሁ? ለእኔ እስካሁንም እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር ብሏል፥’ ብለህ እንድትነግርልኝ ወደ ንጉሡ ልልክህ ወደ እኔ ና ብዬ አስጠራሁህ፤ አሁንም ቢሆን ወደ ንጉሡ ፊት መቅረብ እፈልጋለሁ፤ ምንም ዓይነት በደል ከተገኘብኝ ይግደለኝ” አለው።
ኢሳይያስም “በቤተ መንግሥቱ ምን አዩ” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “ሁሉን ነገር አይተዋል፤ በግምጃ ቤቱ ካለው ሀብት ሁሉ ለእነርሱ ያላሳየኋቸው አንድም ነገር የለም” አለ።
“በአንተ ላይ ኃጢአት ስለ ሠሩ ሰማያት በተዘጉ ጊዜ ዝናብም ባልዘነበ ጊዜ፥ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህንም ቢጠሩ፥ ባሠቃየሃቸውም ጊዜ ከኃጢአታቸው ቢመለሱ፥
ከዔላም ልጆች ወገን የነበረ፥ የይሒኤል ልጅ ሽካንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለአምላካችን ታማኞች አልሆንም፥ የምድሪቱን ሕዝቦች እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፥ አሁንም ግን በዚህ ነገር ለእስራኤል ተስፋ አለ።
እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፥ እግዚአብሔርም ራርቶ አደርግባችኋለሁ ብሎ የተናገረውን ክፉ ነገር አላደረገውም።
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሓ ይገቡ ዘንድና ለንስሓ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ተናገርሁ።
ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ኃጢአት ሠርቼአለሁ፤ የጌታን ትእዛዝና የአንተን ቃል አልጠበቅሁም፤ ሕዝቡን በመፍራት የፈለጉትን ሁሉ አደረግሁ፤
ሳኦልም መልሶ፥ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለጌታ እሰግድ ዘንድ እባክህ አብረኸኝ ተመለስ” አለው።