ምሳሌ 27:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደረቁ ሣር ተወግዶ፣ አዲሱ ብቅ ሲል፣ በየኰረብታው ላይ ያለው ሣር ተሰብስቦ ሲገባ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደረቅ ሣር ታጭዶ አዲስ ሣር ሲበቅል፥ በተራራ ላይ ያለው ሣርም ሲሰበሰብ፥ |
እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት ለእናንተ ዋስትና ለመቆም በምጽጳ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።”
አይሁድ ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፤ ወደ ይሁዳም አገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፤ ወይንና የበጋንም ፍሬ እጅግ ብዙ አከማቹ።