ምሳሌ 25:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኀጥእ ፊት የሚወድቅ ጻድቅ እንደደፈረሰ ምንጭና እንደ ተበከለ ኩሬ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣ እንደ ደፈረሰ ምንጭ ወይም እንደ ተበከለ የጕድጓድ ውሃ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክፉን ሰው ጠባይ የሚወርስ ደግ ሰው የደፈረሰን ምንጭ ወይም የተመረዘን ኲሬ ይመስላል። |
የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።
ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም።”