ተመለከትሁና አሰብሁ፥ አየሁትና ተግሣጽን ተቀበልሁ።
ያየሁትን ነገር አወጣሁ፣ አወረድሁ፤ ካስተዋልሁትም ትምህርት አገኘሁ፤
ይህን በተመለከትኩ ጊዜ ስለ እርሱ አስባለሁ፤ ከተመለከትኩትም ነገር ትምህርትን ገበየሁ።
የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ የጋለ ነው፤ እርሱን ለሚታመኑት ጋሻ ነው።
ሰው ምንድነው ታከብረው ዘንድ፥ ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ፥
በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፥ ጌታ ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።
እነሆም፥ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፥ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፥ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሶአል።
ትንሽ መተኛት፥ ትንሽ ማንቀላፋት፥ ለማረፍ እጅህን ታጥፋለህ፥
ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰላሰለች ትጠብቀው ነበር።
ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም እነዚህን ነገሮች ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።
ይህ ሁሉ ነገር እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፤ የተጻፈው ግን በዘመናት መጨረሻ ለምንገኘው ለእኛ ተግሣጽ ነው።
እነርሱ ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛም እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ ሆኑልን።
ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም በማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አይደረግም።”
ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።
አስተዋዮች ቢሆኑ፥ ይህንን በተገነዘቡ፥ ፍጻሜያቸውንም ባሰቡ ነበር!