ለክፉ ሰው የወደፊት ተስፋ የለውምና፥ የክፉዎች መብራት ይጠፋልና።
ግፈኛ ተስፋ የለውምና፤ የክፉዎችም መብራት ድርግም ብላ ትጠፋለች።
ዐመፀኛ ሰው “ወደ ፊት ይህን አገኛለሁ” ብሎ ተስፋ የሚያደርገው ነገር የለውም።
ዘመኑ ለክፉዎች አይሆንምና የኃጥኣንም መብራት ይጠፋልና።
ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን ዋጋው ከንቱ ነገር ይሆናልና።
“የክፉዎች መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቁጣው መከራ የከፈላቸው፥
በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል የሚያቃጥል ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።
እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና።
ጌታ ተገለጠ፥ ፍርድንም አከናወነ፥ ክፉ በገዛ እጆቹ ሥራ ተጠመደ።
ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።
ጠማማ ልብ ያለው መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል።
አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።
ትዕቢተኛ ዓይንና ደፋር ልብ የኀጥኣንም እርሻ ኃጢአት ነው።
በእውነት መጨረሻህ ያምራልና፥ ተስፋህም አይጠፋምና።
በደለኞች ወዮላቸው፤ ጥፋት ይመጣባቸዋል፤
ሞኞቹ ብልሆቹን ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነውና ከዘይታችሁ ስጡን’ አሉአቸው።
የመንግሥቱ ልጆች ግን ውጪ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
የገዛ ነውራቸውን አረፋ የሚደፍቁ እየባሰ የሚሄድ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተዘጋጀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።