ምሳሌ 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብታም ለመሆን አትድከም፥ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብት ለማግኘት ስትል ራስህን አታድክም፤ ሐሳብህን የመግታት ጥበብ ይኑርህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመበልጸግ አትድከም፤ ከዚህ ዐይነት ስግብግብነት ለመራቅ ጥበበኛ ሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ድሃ ስትሆን ከባለጠጋ ጋር አትወዳደር። በዐሳብህም ራቅ። |
ተናገር፥ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰውም ሬሳ እንደ ጉድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።’ ”
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤