ምሳሌ 23:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያሰራጫል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጨረሻው እንደ እባብ ይነድፋል፤ እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻ እንደ እባብ ይነድፍሃል፤ እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጭብሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጨረሻም እባብ እንደ ነደፈው፥ የእፉኝትም መርዝ እንደ ተሰራጨበት ትዘረጋለህ። |
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤