አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።
ምሳሌ 23:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት ሲቀላ፥ መልኩም በብርጭቆ ሲያንጸባርቅ፥ እየጣፈጠም ሲገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልኩ ቀይ ሆኖ፣ በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣ ሰተት ብሎ በሚወርድበትም ጊዜ፣ ወደ ወይን ጠጅ ትክ ብለህ አትመልከት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ምንም እንኳ መልኩ በጣም ቀይ ሆኖ በብርጭቆ ውስጥ ቢያንጸባርቅ ሲጠጡትም ሰተት ብሎ ቢገባ የወይን ጠጅ አያስጐምጅህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ጽዋዎችና ወደ ብርሌ ዐይንህን ብትሰጥ፥ በኋላ እንደ ግንብ ዕራቁትህን ትሄዳለህ፤ |
አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።
ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጉለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፥ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤