ምሳሌ 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነት መጨረሻህ ያምራልና፥ ተስፋህም አይጠፋምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለነገ ርግጠኛ አለኝታ ይኖርሃል፤ ተስፋህም ከንቱ አይሆንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ብታደርግ የወደፊት ኑሮህ የተቃና ይሆናል፤ ተስፋህም አያቋርጥም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብትጠብቃቸው ዘመድ ይሆኑሃል፥ ተስፋህም አትጠፋም። |
ለእናንተ የማስበውን አሳብ እኔ ጠንቅቄ አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ለወደፊት የሠመረ ጊዜና ተስፋ ልሰጣችሁ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።
አብርሃም ግን ‘ልጄ ሆይ! አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም ነገሮችህን እንደተቀበልህ አስብ፤ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል፤ አንተም ትሠቃያለህ።
ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በምንም ዓይነት ነገር አላፍርም፤ ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ እንደ ወትሮው እንዲሁ አሁንም በሥጋዬ ይከብራል ብዬ በሙሉ ድፍረት እናገራለሁ።