Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 29:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ለእናንተ የማስበውን አሳብ እኔ ጠንቅቄ አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ለወደፊት የሠመረ ጊዜና ተስፋ ልሰጣችሁ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጣችሁ፣ የሰላም ሐሳብ እንጂ ለክፉ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለ እናንተ ያለኝን ዕቅድ የማውቅ እኔ ነኝ፤ ይህም ዕቅድ ክፋትን ሳይሆን ሰላምን በማስገኘት እናንተ በተስፋ የምትጠብቁት መልካም ነገር የሚፈጸምበት ነው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ለእ​ና​ንተ የማ​ስ​ባ​ትን አሳብ እኔ አው​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፍጻ​ሜና ተስፋ እሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሰ​ላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፥ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 29:11
38 Referencias Cruzadas  

እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል? የወደደውንም ያደርጋል።


የጌታ ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው።


ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።


እግዚአብሔር የሚናገረውን እሰማለሁ፥ ወደ እብደታቸው ካልተመለሱ በቀር ጌታ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ይናገራልና።


እሾህና ኩርንችት ቢያበቅልብኝ፥ እኔ አልቈጣም፥ በእነርሱ ላይ ተራምጄ አቃጥላቸዋለሁ።


“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም በደኅንነት ይቀመጣል፥ እርሱም፦ ‘ጌታ ጽድቃችን ነው’ በሚለው በዚህ ስም የሚጠራ ይሆናል።


“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የላክሁትን የይሁዳን ምርኮ በበጐነት እመለከተዋለሁ።


“አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል ጌታ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረኩበት አገር አድናለሁና፤ ያዕቆብም ይመለሳል ያርፋልም በደኅንነትም ይቀመጣል፤ እርሱንም ማንም አያስፈራራውም።


ነገር ግን ጌታ አምላካቸውንና የማስነሣላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ።


እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸዋለሁም፤ እጅግም የበዛ ሰላምንና እውነትን እገልጥላቸዋለሁ።


ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።


ስለዚህ እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል አርቄ ብወስዳቸውም፥ በአገሮች መካከል ብበትናቸውም፥ በሄዱባቸው አገሮች በዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ።


ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።


ነገር ግን የጌታን አሳብ አያውቁም፥ ምክሩንም አያስተውሉም፤ እንደ ነዶ በአውድማ አከማችቷቸዋልና።


ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።


አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos