La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 22:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ራሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ይርቃል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል።

Ver Capítulo



ምሳሌ 22:5
15 Referencias Cruzadas  

እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፥ በመረብም ላይ ይሄዳል።


በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል የሚያቃጥል ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።


በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።


መልካም እውቀት ሞገስን ይሰጣል፥ የወስላቶች መንገድ ግን ሸካራ ናት።


አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል።


የታካች መንገድ እንደ እሾህ አጥር ናት፥ የጻድቃን መንገድ ግን የተደላደለች ናት።


የቅኖች መንገድ ከክፋት መራቅ ነው፥ መንገዱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታል።


ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል።


የትሕትናና ጌታን የመፍራት ውጤት ሀብት፥ ክብርና ሕይወት ናቸው።


ክፉ ሰው በጥፋቱ ይጠመዳል፥ ጻድቅ ግን ደስ ይለዋል፥ እልልም ይላል።


የክፋት መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥ እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።


ጌታ አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድና አሽክላ፥ ለጎናችሁም መቅሠፍት፥ ለዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ ጌታ አምላካችሁ ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንደማያሳድዳቸው ፈጽማችሁ እወቁ።


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንደማያደርግ እናውቃለን፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን ይጠብቃል፤ ክፉውም አይነካውም።