Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 16:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የቅኖች መንገድ ከክፋት መራቅ ነው፥ መንገዱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የቅኖች ጐዳና ከክፋት የራቀ ነው፤ መንገዱንም የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ደጋግ ሰዎች ክፋት በሌለበት መንገድ ይሄዳሉ፤ አካሄዱን የሚያሳምር ሕይወቱን ይጠብቃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 16:17
16 Referencias Cruzadas  

በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፥ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐን ያልሆኑ አያልፉበትም፥ የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ግን ያልፉበታል፤ ተጓዦች ሆኑ፥ ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።


ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል።


ያለ ነውር የሚመላለስ ተማምኖ ይሄዳል፥ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።


የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ለመፈተን በዓለም ሁሉ ላይ ከሚመጣው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።


ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚያደርሰውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ ሳለ፥ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።


እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑት ጋር ነን እንጂ፥ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ ጋር አይደለንም።


ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።


እስከ መጨረሻው የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።


አሁንም ሳትሰናከሉ ሊጠብቃችሁ፥ በክብሩ ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ ሊያቆማችሁ ለሚችለው፤


ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።


ከሁሉ አስበልጠህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት ምንጭ እርሱ ነውና።


አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።


እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios