ምሳሌ 21:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፥ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው ለጻድቅ፣ ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደጋግ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በክፉ ሰዎች ላይ ይደርሳል፤ በቀጥተኛ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በእምነተ ቢሶች ላይ ይመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ በጻድቅ ዘንድ የተናቀ ነው፥ ኃጥእም የጻድቅ ቤዛ ነው። |
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።