ተድላ የሚወድድ ድሀ ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትንም የሚወድድ ሀብታም አይሆንም።
ቅንጦትን የሚወድድ ይደኸያል፤ የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድድም ባለጠጋ አይሆንም።
ቅንጦትን የሚወድ ሰው ይደኸያል፤ የወይን ጠጅንና ቅባትን የሚወድድ ሰው ምንጊዜም አይበለጽግም።
ደስታን የሚወድድ ድሃን ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትን የሚወድድም ባለጠጋ አይሆንም።
ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፥ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።
የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፥ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ያሟጥጠዋል።
ከወይን ጠጅ ጠጪዎች ጋር አትቀመጥ እንዲሁም ሥጋ ከማይጠግቡ ጋር፥
ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉና፥ የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና።
ለዚህ ዓለም ደስታ የምትኖር መበለት ግን በሕይወትዋ ሳለች እንኳ የሞተች ናት።
ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተወጠሩ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፥