እርሱ፥ እንደ ንጋት ብርሃን እንደ ማለዳ ፀሐይ አወጣጥ፥ ደመና በሌለበት ማለዳ እንደምታበራ የብርሃን ጸዳል፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።
ምሳሌ 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፍርድ ወንበር የተቀመጠ ንጉሥ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ ይበትናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ለፍርድ ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ አበጥሮ ይለያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍርድ ዙፋን ላይ የተቀመጠ ንጉሥ ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ አበጥሮ የሚያውቅ ዐይን አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነተኛ ንጉሥ በዙፋኑ በተቀመጠ ጊዜ በዐይኖቹ ፊት ምንም ክፉ አይቃወመውም። |
እርሱ፥ እንደ ንጋት ብርሃን እንደ ማለዳ ፀሐይ አወጣጥ፥ ደመና በሌለበት ማለዳ እንደምታበራ የብርሃን ጸዳል፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።
ሰሎሞን ችሎት ተቀምጦ የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበትም የዙፋን አዳራሽ ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ሳንቃ የተለበደ ነበር።