ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በጌታ ስም እንዲህ ሲል ማለ፦ “አዶንያስ ይህን በማቀዱ በሕይወቱ እንዲከፈል ባላደርግ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ በበለጠም ይቅጣኝ!
ምሳሌ 20:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤ የሚያስቈጣውም ሰው ሕይወቱን ለመከራ ይዳርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ ቊጣ እንደሚያገሣው አንበሳ ያስፈራል፤ የእርሱንም ቊጣ የሚያነሣሣ በራሱ ላይ የሞት ፍርድ እንደ ፈረደ ይቈጠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሥ ቍጣ ከአንበሳ ቍጣ አያንስም፤ የሚያስቈጣውም ሰው የራሱን ነፍስ ይበድላል። |
ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በጌታ ስም እንዲህ ሲል ማለ፦ “አዶንያስ ይህን በማቀዱ በሕይወቱ እንዲከፈል ባላደርግ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ በበለጠም ይቅጣኝ!
እግዚአብሔር በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ አስቀምጦ መንግሥቴን የጸና አድርጎልኛል፤ ይህን መንግሥት ለእኔና ለዘሮቼ በመስጠት ቃሉን ጠብቆአል፤ እንግዲህ አዶንያስ በዚህ በዛሬው ቀን በሞት እንደሚቀጣ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ!”
በኃጢአታቸው የተነሣ ሕይወታቸውን አሳልፈው ለሞት የሰጡትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፋችሁ ለመሠዊያ መለበጫ አድርጓቸው፤ በጌታ ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፥ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።”