ምሳሌ 19:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፥ የጌታ ምክር ግን እርሱ ይጸናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ብዙ ነገር ያቅዳሉ፤ ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰው ልብ ብዙ ዐሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል። |
አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።
ለእናንተም፦ እንደ አሕዛብና እንደ ምድር ወገኖች እንሆናለን፥ እንጨትና ድንጋይም እናመልካለን የሚል ከልባችሁ የወጣ አሳብ አይፈጸምላችሁም።
ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።
አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።