በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ እነርሱንም ረዳቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተላልፈው ተሰጡ።
ምሳሌ 16:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃልን የሚያዳምጥ መልካም ነገርን ያገኛል፥ በጌታ የታመነ ምስጉን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክርን የሚሰማ ይለመልማል፤ በእግዚአብሔርም የሚታመን ብፁዕ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚሰጠው ምክር ትኲረትን የሚሰጥ ይበለጽጋል፤ በእግዚአብሔርም የሚተማመን የተባረከ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሥራ ዐዋቂ የሆነ መልካም ነገርን ያገኛል፤ በእግዚአብሔርም የታመነ ብፁዕ ነው። |
በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ እነርሱንም ረዳቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተላልፈው ተሰጡ።
ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።