ምሳሌ 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው መንገድ ሁሉ በዐይኖቹ ፊት ንጹሕ ነው፥ ጌታ ግን መንፈስን ይመዝናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰው መንገዱ ሁሉ ንጹሕ መስሎ ይታየዋል፤ መነሻ ሐሳቡ ግን በእግዚአብሔር ይመዘናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል የሆነ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዓላማውን ይመዝናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የትሑት ሰው ሥራ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው፥ |
እነሆ፥ ይህን አላውቀውም ብትል፥ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ሥራው አይመልስለትምን?
እንዲህም አላቸው “ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሰት ነውና።
“በትያጥሮንም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዐይኖች ያሉት በምድጃም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፦
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው።