በሬ በሌለበት ስፍራ እህል አይገኝም፥ ብዙ ሲሳይ ግን በበሬዎች ኃይል ነው።
በሬዎች በሌሉበት በረቱ ባዶ ይሆናል፤ በበሬ ጕልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል።
የምታርስባቸው በሬዎች ከሌሉህ ጐተራህ ባዶ ይሆናል። በሬዎች ካሉህ ግን ጐተራህ በእህል የተሞላ ይሆናል።
በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤ ብዙ እህል ግን በበሬዎች ኀይል ይገኛል።
ጉልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ በእርሱ ትታመናለህን? አድካሚ ሥራህን ለእርሱ ትተዋለህን?
ላሞቻቸንም የሰቡ ይሁኑ፥ ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ አይኑረው፥ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይኑር፥
በድሆች እርሻ ላይ ብዙ ሲሳይ አለ፥ ከፍርድ መጉደል የተነሣ ግን ይጠፋል።
በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፥ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።
የታመነ ምስክር አይዋሽም፥ የሐሰት ምስክር ግን በሐሰት ይናገራል።
“እኔ በከተማችሁ ሁሉ ራብን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣት አመጣባችኋለሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።