ምሳሌ 13:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፥ ኀጥእ ግን ያሳፍራል ያስነውራልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ ክፉ ሰው ግን ኀፍረትንና ውርደትን ያመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች ሐሰትን ይጠላሉ፤ የክፉዎች ሰዎች ንግግር ግን አሳፋሪና አስነዋሪ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤ ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም። |
ያመለጡት ተማርከው በሄዱባቸው በአሕዛብ መካከል ሆነው ያስታውሱኛል፤ ምክንያቱም ከእኔ በራቀው አመንዝራ ልባቸውና፥ ጣዖቶቻቸውን በተከተሉ በአመንዝራ ዐይኖቻቸው ተሰብሬአለሁና፥ በክፉ ስራቸውና በርኩሰታቸውም ሁሉ ራሳቸውን ይጸየፋሉ።
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”