ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው።
የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል።
የጠቢባን ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ሕይወትህ በአደጋ ላይ ቢወድቅ እንኳ እንድታመልጥ ይረዳሃል።
የብልህ ሰው ሕግ የሕይወት ምንጭ ነው። ማስተዋል የሌለው ግን በኀጢአት ይሞታል።
የሞት ገመዶች ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።
የሞት ገመዶች ጠፍረው ያዙኝ፥ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፥
የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ማፍለቂያ ናት፥ የክፉዎች አፍ ግን ዐመፅን ይሸፍናል።
ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ ጌታን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው።
በታች ካለው ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ የሕይወት መንገድ አስተዋዩን ሰው ወደ ላይ ይወስደዋል።
የቅኖች መንገድ ከክፋት መራቅ ነው፥ መንገዱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታል።
ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፥ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው።
በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ ጌታንም በመፍራት ሰው ከክፋት ይመለሳል።
ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና።
ደም እንዳላፈስና በገዛ እጄ እንዳልበቀል ዛሬ ስለ ጠበቅሽኝ ስለ በጎ ሐሳብሽ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ።