ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፥ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው።
ሰነፍ ዐድኖ ያመጣውን እንኳ አይጠብስም፤ ትጉህ ሰው ግን ለንብረቱ ዋጋ ይሰጣል።
ሰነፍ ከሆንክ የምትመኘውን ማግኘት አትችልም፤ በትጋት ከሠራህ ግን ትበለጽጋለህ።
ታካች ሰው አድኖ አይዝም። ንጹሕ ሰው ግን ክቡር ሀብት ነው።
በጻድቅ ዘንድ ያለው ጥቂት ነገር ከብዙ ክፉዎች ሀብት ይበልጣል።
የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፥ የትጉ እጅ ግን ሀብታም ታደርጋለች።
ጻድቅ ለባልንጀራው መንገዱን ያሳያል፥ የኀጥኣን መንገድ ግን ታስታቸዋለች።
የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፥ አንዳችም አታገኝም፥ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች።
ጌታን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል።
በጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር በዓመፅ ከሚገኝ ከብዙ ትርፍ ይሻላል።
ሰውነትህም ቢጎመጅ፥ በጉሮሮህ ላይ ካራ አድርግ።
መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፥ እንዲሁ ሰነፍ ሰው በአልጋው ላይ ይገላበጣል።
ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፥ ወደ አፉም መመለስ ለእርሱ ድካም ነው።