ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።
ምሳሌ 12:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውሸተኛ ከንፈር በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሐሰተኛ ከንፈርን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ደስ ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሐሰተኛ አንደበትን ይጸየፋል፤ በእውነተኞች ሰዎች ግን ይደሰታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው። |
ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።
ነገር ግን የሚመካው፦ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ ጌታ መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ ነገሮች እነዚህ ናቸውና፥ ይላል ጌታ።”
እፍኝ ገብስና ቁራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ፥ ውሸት ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ፥ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት በመግደል፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን ነፍሳት በሕይወት በማትረፍ በሕዝቤ ፊት አርክሳችሁኛል።
ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”