ክፉ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋው ይቈረጣል፥ የኃያል አለኝታም ይጠፋል።
ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ከንቱ ትሆናለች፤ በኀይሉ የተመካበትም ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል።
ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋውም አብሮት ይሞታል፤ በኀይሉ መመካቱም አብሮት ይጠፋል።
ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥ የክፉዎች ትምክሕታቸው ግን ትጠፋለች።
የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥ የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥ ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”
ክፉ ሰውም አይቶት ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፥ የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች።
ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል፥ ያንጊዜ እቅዶቹ በሙሉ ይጠፋሉ።
የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፥ የክፉዎች ተስፋ ግን ይጠፋል።
የጌታ መንገድ ያለ ነውር ለሚሄድ አምባ ነው፥ ክፋትን ለሚያደርጉ ግን ጥፋት ነው።
ጻድቅ ከጭንቀት ይድናል፥ ክፉ ግን የእርሱን ቦታ ይወስዳል።
ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።
በገዳይህ ፊትም፦ “እኔ አምላክ ነኝ” ትላለህን? ቢሆንም አንተ በገዳይህ እጅ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።