መልካም ምክር በሌለበት ሕዝብ ይወድቃል፥ በአማካሪዎች ብዛት ግን ዋስትና ይገኛል።
በአመራር ጕድለት መንግሥት ይወድቃል፤ የመካሮች ብዛት ግን ድልን ርግጠኛ ያደርጋል።
አማካሪ የሌለው መንግሥት ይወድቃል፤ ብዙ አማካሪዎች ሲኖሩ ግን ዋስትና ይገኛል።
መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።
አሁንም ነዪ፥ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኝ እመክርሻለሁ።
የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በጌታ ፊት ክፉ አደረገ፤ አባቱም ከሞተ በኋላ የአባቱ አመካሪዎች መጥፊያው እስኪሆኑ ድረስ አማከካሪዎቹ ነበሩና።
ምክር ከሌለች የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል፥ መካሮች በበዙበት ግን ይጸናል።
ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፥ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው።
አሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።
በመልካም አመራር ጦርነትን ትመራለህ፥ ብዙ ምክር ባለበትም ድል ይገኛል።