ፊልጵስዩስ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአምላካችንና ለአባታችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአምላካችንና ለአባታችን ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአባታችንና ለአምላካችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአባታችን ለእግዚአብሔር ለዘለዓለሙ ምስጋና ይሁን አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላካችንና ለአባታችንም እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። |
እርሱ ብቻ አዳኛችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ክብር፥ ግርማ፥ ኃይልና ሥልጣን ከዘመናት ሁሉ በፊት፥ አሁንም እስከ ዘለዓለምም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።
በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።
“አሜን ውዳሴ፥ ክብር፥ ጥበብ፥ ምስጋና ገናናነት፥ ክብር ኃይልና ብርታት ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን! አሜን።” አሉ።