አብድዩ 1:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም የእስራኤል ልጆች የጦር ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፥ በስፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከነዓን ያለው ይህ የእስራኤል ስደተኞች ወገን፣ እስከ ሰራፕታ ያለውን ምድር ይወርሳል፤ በሰፋራድም ያሉ የኢየሩሳሌም ስደተኞች፣ የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስደት ላይ የነበሩት የሰሜን እስራኤል ሕዝብ ሖላ ከሚባል አገር ተመልሰው የከነዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ፤ በሰፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ስደተኞች በስተ ደቡብ ያሉትን ከተሞች ይይዛሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም የእስራኤል ልጆች የጭፍራቸው ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፤ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች እስከ ኤፍራታ ድረስ የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም የእስራኤል ልጆች የጭፍራቸው ምርኮ የከነዓንን ስፍራ ሁሉ እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳል፥ በስፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ምርኮኞች የደቡብን ከተሞች ይወርሳሉ። |
በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳሉ፤ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና በብንያም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች፥ በደጋውም ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ፥ ምስክሮችንም ጠርተው በውሉ ሰነድ ላይ ፈርመው ያትሙታል፥ ይላል ጌታ።”
በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ መንጋውን በሚቆጥረው ሰው እጅ ሥር እንደገና ያልፋሉ፥ ይላል ጌታ።
በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች እንዲሆኑ ከዘሩ ላለመውሰድ፥ የያዕቆብንና የባርያዬን የዳዊትን ዘር እኔ ደግሞ እጥላለሁ። እኔ ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፥ እምራቸዋለሁምና።”
ሰዎችን፥ ሕዝቤን እስራኤልን፥ በእናንተ ላይ አስሄዳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይወርሱሻል ርስትም ትሆኛቸዋለሽ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ልጅ አልባ አታደርጊአቸውም።