አብድዩ 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 የደቡብም ሰዎች የዔሳውን ተራራ፥ የቆላውም ሰዎች ፍልስጥዔማውያንን ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንም አገር የሰማርያንም አገር ይወርሳሉ፥ ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 የኔጌብ ሰዎች፣ የዔሳውን ተራራ ይይዛሉ፤ ከተራራው ግርጌ ያሉ ሰዎችም፣ የፍልስጥኤማውያንን ምድር ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንና የሰማርያንም ዕርሻ ይይዛሉ፤ ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “ከይሁዳ በስተደቡብ ያሉ ሕዝቦች የኤዶምን ምድር ይወርሳሉ፤ በምዕራብ ተራራዎች ግርጌ በሚገኘው ቆላማ ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች የፍልስጥኤምን ምድር ይይዛሉ፤ የኤፍሬምንና የሰማርያንም ግዛት ይወስዳሉ፤ የብንያም ሰዎችም የገለዓድን ምድር ይወርሳሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የደቡብም ሰዎች የዔሳውን ተራራ፥ የቆላውም ሰዎች ፍልስጥኤማውያንን ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንም ተራራ፥ የሰማርያን፥ የብንያምንና የገለዓድን ሀገር ይወርሳሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የደቡብም ሰዎች የዔሳውን ተራራ፥ የቈላውም ሰዎች ፍልስጥዔማውያንን ይወርሳሉ፥ የኤፍሬምንም አገር የሰማርያንም አገር ይወርሳሉ፥ ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል። Ver Capítulo |