አብድዩ 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ፥ አንተ እጅግ ተንቀሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፤ እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኤዶምን እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በአሕዛብ መካከል ደካማ አደርግሃለሁ፤ እጅግም የተናቅህ ትሆናለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ፤ አንተ እጅግ ተንቀሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ፥ አንተ እጅግ ተንቀሃል። |
ከመንግሥታት ሁሉ ይልቅ የተዋረደች ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲያ በሕዝቦች ላይ ከፍ ከፍ አትልም፤ በሕዝቦችም መካከል እንዳይገዙ አሳንሳቸዋለሁ።