ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤
አብድዩ 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳር ቆመህ በተመለከትክበት ቀን፥ አሕዛብ ሀብቱን በማረኩበት፥ ባእዳን በበሩ በገቡበት፥ በኢየሩሳሌምም ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን አንተም እንደ እነርሱ ነበርህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዶች ሀብቱን ዘርፈው ሲሄዱ፣ ባዕዳንም በበሮቹ ሲገቡ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ ሲጣጣሉ፣ በዚያ ቀን ገለልተኛ ሆነህ ተመለከትህ፣ አንተም ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆንህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻቸው በሮቻቸውን ሰባብረው፥ ሀብታቸውን ሁሉ በዘረፉበት ቀን፥ አንተ በዳር ቆመህ ትመለከት ነበር፤ አንተ እኮ ኢየሩሳሌምን በዕጣ ከተከፋፈሉአት ሰዎች በምንም አትሻልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቱ አንጻር በቆምህ ቀን፥ አሕዛብ ጭፍራውን በማረኩበት፥ እንግዶችም በበሩ በገቡበት፥ በኢየሩሳሌምም ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን አንተ ደግሞ ከእነርሱ እንደ አንዱ ነበርህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊቱ አንጻር በቆምህ ቀን፥ አሕዛብ ጭፍራውን በማረኩበት፥ እንግዶችም በበሩ በገቡበት፥ በኢየሩሳሌምም ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን አንተ ደግሞ ከእነርሱ እንደ አንዱ ነበርህ። |
ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው፤
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ለኤዶምያስ አሳልፈው ለመስጠት መላውን ሕዝብ ማርከው ወስደዋልና ስለ ሦስት የጋዛ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በምርኮ የሄዱትን ሕዝብ ሁሉ ለኤዶምያስ አሳልፈው ሰጥተዋልና፥ የወንድማማቾችንም ቃል ኪዳን አላስታወሱምና ስለ ሦስት የጢሮስ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።
ሆኖም ግን ተማርካ ተወሰደች፤ ሕፃናቶችዋ በመንገዶች ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፤ በከበርቴዎችዋ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።