Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አብድዩ 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ነገር ግን በወንድምህ የመከራ ቀን ልትደሰት፥ በጥፋታቸውም ቀን በይሁዳ ልጆች መጥፋት ደስ ሊልህ፥ በጭንቀታቸውም ቀን በትዕቢት ልትናገር አይገባም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፣ በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑ ሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤ በጭንቀታቸውም ቀን፣ በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በይሁዳ አገር በሚኖሩ ወንድሞችህ ላይ በደረሰው መከራ፥ ልትደሰት ባልተገባህም ነበር፤ በጥፋታቸው ቀን ሐሤት ልታደርግና በጭንቀታቸውም ቀን በእነርሱ ላይ ልትታበይ ባልተገባህም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በጠ​ላት ቀን ወን​ድ​ም​ህን ዝቅ አድ​ር​ገህ ትመ​ለ​ከ​ተው ዘንድ፥ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭ​ን​ቀ​ታ​ቸ​ውም ቀን በት​ዕ​ቢት ትና​ገር ዘንድ ባል​ተ​ገ​ባህ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ነገር ግን በመከራው ቀን ወንድምህን ትመለከት ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በይሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭንቀትም ቀን በትዕቢት ትናገር ዘንድ አይገባህም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




አብድዩ 1:12
27 Referencias Cruzadas  

አሁንም፦ “ትርከስ፥ ዓይናችን በጽዮን ላይ ይሁን” የሚሉ ብዙ አሕዛብ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል።


የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በመሆኑ እንደተደሰትህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተ፥ ኤዶም ሁሉና ሁለንተናዋ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል፥ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም።


እጅግ በመኩራራት አትናገሩ፥ የእብሪትም ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፥ ጌታ አምላክ አዋቂ ነውና፥ በእርሱም ሥራዎች ይመዘናሉ።


ከንቱና የትዕቢት ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት ለጥቂት ያመለጡትን ሰዎች በሥጋ ሴሰኛ ምኞት በማታለል ያስታሉ።


እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ የሚያማርሩ፥ ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው የትዕቢት ቃልን ይናገራል፤ለጥቅማቸው ሲሉ ሰዎችን ያደንቃሉ።


ጌታ ግን ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።


አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፥ ክፉዎች ይፈሩ በሲኦልም ዝም ይበሉ።


ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፥ የክፋተኞች ጉባኤም አገተኝ፥ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።


“በሚጠላኝ መጥፋት ደስ ብሎኝ ክፉ ነገርም ባገኘው ጊዜ ሐሤት አድርጌ እንደሆነ፥


ታላቅ ነውርንና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።


እንዲሁም ምላስ ትንሽ የሰውነት ክፍል ሆና ሳለች በታላላቅ ነገሮች ትኩራራለች፤ ትልቅ ጫካ በትንሽ እሳት እንዴት ተቃጥሎ እንደሚጠፋ አስተውሉ፤


ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ እንዲህ እያለ አለቀሰላት፤


ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።


አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤


እንደ ጐሽ አጠነከርከኝ፥ በአዲስ ዘይትም ቀባኸኝ።


እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።


ክፋትን ወደ ጠላቶቼ ይመልሳታል፥ በእውነትህም አጥፋቸው።


የፊተኞች ሰዎች እንደ ደነገጡ፥ እንዲሁ የኋለኞች ሰዎች ስለ ዘመኑ ይደነቃሉ።


በእኔ ላይ ተሰበሰቡ ደስም አላቸው፥ ግፈኞች በእኔ ላይ ተሰበሰቡ እኔም አላወቅሁም፥ መቦጫጨቃቸውን አላቆሙም።


ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ።


በእስራኤል ተራሮች ላይ “ፈርሰዋል እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ እኔ ጌታ እንደ ሰማሁት ታውቃለህ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios