ዘኍል 36:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ሰው የአባቶቹን ርስት እንዲወርስ፥ ከማናቸውም ከእስራኤል ልጆች ነገድ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአባትዋ ነገድ ባል ታግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ እስራኤላዊ የየአባቶቹን ርስት መውረስ ስላለበት፣ በማንኛውም የእስራኤል ነገድ ውስጥ ርስት የምትወርስ የትኛዪቱም ሴት፣ ከአባቷ ነገድ ወገን የሆነውን አንዱን ማግባት አለባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስራኤላዊ ነገድ መካከል ርስት የተካፈለች ማንኛይቱም ሴት ከዚያው ነገድ የሆነ ወንድ ማግባት ይኖርባታል፤ በዚህ ዐይነት እያንዳንዱ እስራኤላዊ የቀድሞ አባቶቹን ርስት በይዞታው ማቈየት ይችላል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ሰው የአባቶቹን ርስት ይወርስ ዘንድ፥ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ፥ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአባቷ ነገድ ባል ታግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ሰው የአባቶቹን ርስት ይወርስ ዘንድ፥ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ ርስት ያላት ሴት ልጅ ሁሉ ከአባትዋ ነገድ ባል ታግባ። |