ዘኍል 36:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም የሰለጰዓድ ሴት ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። |
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ ተሳዳቢውንም ከሰፈሩ ውጭ አወጡት፥ በድንጋይም ወገሩት። የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለቆችም ቀርበው እንዲህ አሉ፦ “ጌታ በወንድሞቻችን መካከል ርስት እንዲሰጠን ሙሴን አዘዘ፤” ጌታም እንዳዘዘ በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስት ሰጣቸው።