“የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ፥ እኔ አሕዛብን አስነሣባችኋለሁ፥” ይላል ጌታ የሠራዊት አምላክ፤ “እነርሱም ከሐማት መግቢያ ጀምረው እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።”
ዘኍል 34:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሰሜንም ድንበራችሁ ይህ ይሆናል፤ ከታላቁ ባሕር ወደ ሖር ተራራ የወሰን ምልክት ታደርጋላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሜን ድንበራችሁን ከታላቁ ባሕር እስከ ሖር ተራራ ምልክት አድርጉበት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰሜኑ ወሰን የሜዲቴራኒያንን ባሕር በመከተል እስከ ሖር ተራራ ይሆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመስዕም በኩል ወሰናችሁ ከታላቁ ባሕር በተራራው በኩል ይሆንላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰሜንም ዳርቻችሁ ይህ ይሆናል፤ ከታላቁ ባሕር ወደ ሖር ተራራ ምልክት ታመለክታላችሁ። |
“የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ፥ እኔ አሕዛብን አስነሣባችኋለሁ፥” ይላል ጌታ የሠራዊት አምላክ፤ “እነርሱም ከሐማት መግቢያ ጀምረው እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።”
የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምያስን ዳርቻ እያዋሰነ የሚያልፈው ይሆናል፤ የደቡቡም ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤